የአዲስ ዓመት የሰላም ጥሪ ከአገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች

ባሁኑ ወቅት አገራችን ኢትዮጵያ በከባድ ቀውስ ውስጥ ትገኛለች። በትግራይ፣ በአማራ፣ በምዕራብና ደቡብ ኦሮሚያ፣ በሶማሊ፣ በአፋር፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች በሚካሔዱ ግጭቶች ምክንያት በሺሕ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን እየሞቱ ነው። በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ከቀያቸው እየተፈናቀሉ ነው። ሚሊዮኖች የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ ላይ ጥገኛ እየሆኑ ነው። ሕፃናት ልጆቻችን፣ በዕድሜ የገፉ ወገኖቻችን እና ሴቶቻችን በተለየ ሁኔታ ለመከራ ተጋላጭ እየሆኑ፣ ጾታዊ ጥቃትንና ግድያን ጨምሮ የተለያዩ የሰብዓዊ ጥሰቶች ሰለባ በመሆን ላይ ናቸው። ኢኮኖሚያችን በከፍተኛ ደረጃ እየተጎዳ፣ መሠረተ ልማቶች እየወደሙ ነው። ግጭቶችን በሰላም ለመፍታት የምንጠቀምባቸው የሽምግልናና የዕርቅ ባሕላዊና ማኅበራዊ አቅሞቻችንን ለመጠቀም እያደረግን ያለነው ሁለገብ ጥረት እስካሁን ሰላምን ሊያረጋጋጥልን አልቻለም። በመሆኑም ሕዝባችንን ለዘመናት ደግፈው ያቆዩ ማኅበራዊ እሴቶቻችን ሳይቀሩ አደጋ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ። በዚህ ሰብዓዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ በመቆየት የምናገኘው ነገር ቢኖር ያሁኑ ማኅበራዊ ግንኙነታችንን የበለጠ ማሻከር ብቻ ሳይሆን፥ ለመጪው ትውልድም ቂምና ቁርሾ ማውረስን ሊሆን ይችላል።

ይህንን የአዲስ ዓመት የሰላም ጥሪ ለማስተላለፍ የተሰባሰብነው የአገር በቀል ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ ላለፉት በርካታ ወራት በኢትዮጵያ እየተስተዋሉ ያሉ ግጭቶች በአስቸኳይ መቆም አለባቸው፣ ለሰላም ዕድል ሊሰጠው ይገባል በሚል ግልጽ ጥሪ ለማቅረብ የወሰንነው፣ በሚከተሉት ምክንያቶች ነው።
1. ለጦርነቱ መንስዔ የሆኑት የተለያዩ የፖለቲካ ችግሮችን በጦርነት በዘላቂነት ሊፈቱ የማይችሉ በመሆናቸው፣ ይፈታሉ ተብሎ ቢታመን እንኳን መንግሥትን እና መላው የኢትዮጵያን ሕዝብ የሚያስክፍለው ዋጋ የከፋ መሆኑን ከግምት በማስገባት፤
2. ጦርነት እና ግጭቶች ባሉባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች ደኅንነት ጉዳይ ጊዜ የማይሰጥ በመሆኑ፣ በተለይም ሕፃናት፣ ሴቶች እና አረጋውያን ለከፍተኛ አደጋ እየተጋለጡ በመሆናቸው፤
3. ጦርነቱ በተለይም በወጣቱ የማኅበረሰብ ክፍል ላይ እያስከተለ ያለውን እልቂትና ኢኮኖሚያዊ ውድመት፣ እንዲሁም የከፋ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በመመልከት፣ ይህም ኢትዮጵያ ከገባቻቸው ዓለም ዐቀፍ ሥምምነቶች እና ራሷም ማክበር ከምትፈልጋቸው መብቶች ጋር የሚጣረስ በመሆኑ፣ የአገራችንን የልማት ጉዞ ወደኋላ የሚመልስ እና የዘላቂ የዕድገት ግቦችን ለማሳካት ከፍተኛ እንቅፋት የሚፈጥር ሆኖ በማግኘታችን፤
4. ግጭቶቹ እየተስፋፉ በርካታ አካባቢዎችን እያዳረሱ በመሆናቸው እና አሁን መቆም ካልቻለ እጅግ ወደ ከፋ ቀውስ ከመግባታችን በፊት ተነጋግሮ ለመግባባት እና ችግሮቹን ለመፍታት የሚያስችል ሥራ መሠራት ስላለበት፤
5. ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራዎቹ እየተባባሱ ወደ አገር ዐቀፍ እና ንዑስ አህጉራዊ ቀውስ ሊያመሩ የሚችሉ በመሆኑ፣ በተለይም ጦርነቱ በመሠረተ ልማት አገልግሎቶች ላይ እያደረሰ የመጣውን ጉዳት ከግምት በማስገባት፣ ከከፋ ድህነት ለመውጣት በመጣር ላይ የምትገኘው አገራችንን በሌሎች ዘርፎች ላይ ማዋል ያለባት መዋዕለ ነዋይ በጦርነት ላይ ማዋል መጀመርዋ ያለውን ጉዳት በመረዳት፤
6. ጦርነቱ በማኅበራዊ ግንኙነቶች ላይ ያስከተለውን ጉዳት በመገንዘብ በተለይም በኅብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ የሕዝብ ለሕዝብ አዳሪ ቂምና ቁርሾ እያፈሩ ሊመጡ የሚችሉ መሆናቸውን በመመልከት፤
7. ቀውሶቹ በኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ዘላቂ ጥቅም ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እየፈጠሩ፣ ለውጭ ኃይሎች ተፅዕኖ ተጋላጭነታችንን እየጨመሩ በመሆኑ እና የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ኅልውናን የሚፈታተን አደጋ በመደቀኑ፣
8. ለግጭቶቹ ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት አዳጋችነቱ እያደር እያሻቀበ በመምጣቱ፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ የተለያዩ ማኅበረሰብ ክፍሎች ዘንድ የዳበሩ ከጦርነት ወጪ ግጭቶች የሚፈቱባቸው፣ ከጦርነት በኋላም ዕርቅ፣ ሰላምና ፍትሕ ማምጣት የሚችሉ፣ ረቂቅ ልምዶች ስላሉ ለነዚህ የሰላም እሴቶችና ተሞክሮዎች የፖለቲካ ልኂቃኑ ዕድል እንዲሰጡ፣ ሰላምን መገንባት የሚያስችል ቅድመ ሁኔታዎችን እንዲያመቻቹ፤
9. በ2020 የተጀመረውን የአፍሪካ “ነፍጥን ዝም የማሰኘት ዘመቻ” (“Silencing the Guns Campaign”) የሰላም ጥሪዎች እና መግባባት ሊፈጥሩ የሚችሉ ንግግሮችን ማድረግ የሚጀመር በመሆኑ፤
10. የጦርነቱ መባባስ እና እየተስፋፋ መምጣት በተለይም የአገር ውስጥ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን በአግባቡ የመከታተል፣ የመመዝገብ እና የማጣራት ሥራ ላይ እየፈጠረ ያለው ችግርን በመረዳት፣ ይህም በኢትዮጵያ የተለያዩ አስተዳደር ክፍሎች ካለው የግንኙነት አገልግሎት መቋረጥ እና ነባራዊ የደኅንነት ተግዳሮቶች ጋር የተያያዘ መሆኑን በመገንዘብ፤ ስለሆነም ሥማችን ከዚህ በታች የተዘረዘረው አገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እነዚህ ግጭቶች አስቸኳይ መቋጫ ያገኙ ዘንድ ይህንን የአዲስ ዓመት የሰላም ጥሪ እያስተላለፍን በአገራችን የሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችም ግጭቶችን በሰላማዊ መንገዶች ለመፍታት ብሎም ሁለንተናዊ የሰላም ግንባታ ሥራ እና ሁሉን ዐቀፍ ዕርቅ እንዲደረግ የሚያስችሉ ሥራዎች ላይ እንዲያተኩሩ በአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን።

የሰላም ጥሪያችን የተሳካ ይሆን ዘንድ በኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢዎች በግጭቶች ተሳታፊ የሆኑ ወገኖች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከነውጠኛ ግጭቶች፣ ከግጭት አባባሽ ሁኔታዎች እና ከጦርነት ፕሮፓጋንዳዎች በመቆጠብ ለሰላማዊ ንግግሮች ራሳቸውን እንዲያስገዙ እና የብዙኃኑን ደኅንነትና አብሮነት፣ የአገራችንን ሰላምና ሉዓላዊነት ከአደጋ እንዲከላከሉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

እኛም እንደ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ግጭቶችን በሰላማዊ መንገዶች ለመፍታት እና ከዚያም ሁለንተናዊ የሰላም ግንባታ ሥራ እና ሁሉን ዐቀፍ ዕርቅ እንዲሰፍን ለማድረግ የሚያስችሉ ሥራዎችን ለመሥራት ቃል እንገባለን።

ለተጨማሪ መረጃ፣
1. አምሐ መኮንን (ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር፣ የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች)፣ +251911237404
2. ለሚ ሥሜ (ኤግስኪዩቲቭ ዳይሬክተር፣ ኢስት አፍሪካን ኢንሼቲቭ ፎር ቼንጅ (አይፎርሲ))፣ +251904054444

የዚህ የሰላም ጥሪ አቅራቢ ድርጅቶች
1. የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ኅብረት (CEHRO)
2. የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (CARD)
3. ኢስት አፍሪካን ኢንሼቲቭ ፎር ቼንጅ (I4C)
4. የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች
5. ሴታዊት ንቅናቄ
6. የኢትዮጵያ አርታኢያን ማኅበር
7. ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ
8. ኢኒሺዬቲቭ አፍሪካ
9. ፋሚሊ ሰርቪስ አሶሲዬሽን
10. ዓለምዐቀፍ የመነቃቃት አገልግሎት
11. የብሔራዊና ቀጠናዊ ትስስር የጥናት ማዕከል
12. የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር (EWLA)
13. የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል
14. ትምራን
15. ሴንተር ፎር ጀስቲስ
16. ሴንተር ኦፍ ኮንሰርን
17. መልካም አስተዳደር ለአፍሪካ-ምስራቃዊ አፍሪካ
18. የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት (NEWA)
19. ኢንተር አፍሪካ ግሩፕ
20. ጌት ፎር ኦፖርቹኒቲ
21. ኒው ሚሌኒየም


Introducing Our Newest Project Manager Tsion!

Tsion Engdaye has joined the Setaweet Team managing our upcoming Data Project! We asked her to introduce herself a bit below. 

I studied law at AAU and graduated in 2019. I worked in Ethiotelecom as an attorney for a year, and I am also Ezema's youth representative. I used to be a volunteer trainer in Setaweet's Gendershop project two years ago. It's a place I am very familiar with and learned a lot through that project and the Setaweet Circles. I've joined Setaweet hoping the working environment will help me better myself as a feminist and as a professional. 

We're very happy to have such an accomplished woman on our team and look forward to what she can bring to Setaweet. Welcome, Tsion! 


ከሴታዊት አዲስ ቦርድ አባል ሃና ለማ ጋር ጥቂት ቆይታ

የሴታዊት አዲስ ቦርድ አባልን እንተዋወቅ! 

ሀና ለማ እባላለው። የሴቶች መብት ተሟጋች እና የጥናት ተመራማሪ ነኝ። የአዲስ ፓወር ሃውስ ዲጂታል ፌሚኒስት ጋዜጣ አንዷ መስራች ነኝ። በአዲስ ፓወርሃውስ ጋዜጣ በኢትዮጵያ የሴቶች መብት ንቅናቄዎችን እና ተሟጋቾችን ድምፅ ለማጉላት የበኩላችንን እናደርጋለን። ወጣቶችን በፆታ እኩልነት ምክክሮች ላይ ተሳታፊ ማድረግ ደግሞ ሌላኛው ስራችን ነው። በኢንክሉዶቬት የጥናት ተቋም ውስጥ የሥርዓተ -ፆታ ምርምር ሰራተኛ ሆኜ እየሰራሁ እገኛለው። የ1993 የኢትዮጵያ ሴቶች ፖሊሲ ክለሳ ውስጥ ከተሳተፉት ተመራማሪዎች አንዷ ሆኜ መስራቴ ከምኮራባቸው አስተዋፅኦዎች አንዱ ነው። የምሰራቸው እና የምሳተፍባቸው ስራዎች በፆታ እኩልነት ላይ የሚያመጡትን ለውጥ ማየት እንደ አንድ የህይወት አላማዬ እቆጥረዋለው። የሴታዊት የቦርድ አባል መሆንን በደስታ ከተቀብልኩባቸው ምክንያቶች አንዱ፣ ድርጅቱ በሴቶች ሕይወት ላይ ያለውን አዎንታዊ ተፅኖ የማየት ዕድል ማግኘት በመቻሌ ነው።

 

የሴታዊት ቦርድን ለመቀላቀል እንዴት ወሰንሽ? 

ይህንን ያደረኩበት ምክንያት ሴታዊት የምታካሂዳቸው ፕሮጀክቶች እና እንቅስቃሴዎች ሁልጊዜ በጣም የማደንቃቸው ናቸው።  ለምሣሌ ፡- “ምን ለብሳ ነበረ” እና “አሪፍ አባት“ መጀመሪያ በአእምሮዬ የሚመጡት ናቸው። ብዙ ጊዜ ፕሮጀክቶች ሲካሄዱ ፕሮጀክቱን ማስፈፀም ወይም ይህን ያህል ሰው ተረዳ ወይም ያን ያህል ሰው ዝግጅቱ ላይ ነበር ለማለት ነው እንጂ እኔ እንዳየሁት የእውነት የሰዉን አመለካከት መለወጥ ላይ አይሠራበትም። የሴቶች እኩልነትን በቀላሉ የማህበረሰቡን አመለካከት በሚቀይር ሁኔታ በደንብ መሰራት እንዳለበት “በምን ለብሳ ነበረ” እና “አሪፍ አባት” ማየት ችያለሁ። ሰዎች ስለ አስገድዶ መድፈር፣ የአስገድዶ መድፈር ባህል ስላላቸው አመለካከት እና ስለ አባትነት በአጠቃላይ እንዴት አመለካከታቸውን እንደተለወጠ በሴታዊት ማየት ችያለሁ፤ በዚህም የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል እንድሆን ዶ/ር ሲህን ስትጠይቀኝ በጣም ደስተኛ ነው የሆንኩት።

 

አዲስ የሴታዊት ቦርድ አባል እንደመሆንሽ መጠን ስራው ላይ ምን ትጠብቅያለሽ? 

መጀመሪያ ላይ እንደጠቀስኩት የሴቶች መብት ተሟጋች ነኝ ከዛ በተጨማሪም የስርዓተ ፆታ ምርምር ጥናት ሠራተኛ ነኝ እና ሁለቱንም መሆኔ ይጠቅመኛል ብዬ የማስበው ምን አይነት ፌምኒስት ወይም የሴቶች መብት ተሟጋች መሆን አለብን የሚለውን ነገር መረጃ ላይ በተመረኮዘ መልኩ (Evidence-based activity) ለመምራት ነው ። ሴታዊት ላይም በጣም የማነበው ነገር ይህንን ነውየሴታዊት ቦርድ ስቀላቅል ተመሳሳይ የሆነ ዓላማ ወይም አቋም አለን ብዬ ማሰቤ ልክ እንደሆነ ተረድቻለው። 

ሌሎች የቦርድ አባላትም ለሴቶች መብት እስካሁን ድረስ ያደረጉትን አስተዋጽዖ ሆኖም ሰፋ ባለ ሁኔታ  ሃገሪቷ ላይ ላለ ለውጥ መምጣት ከፍ ያለ ተሳታፊነት ያላቸው ናቸው። ከነሱ ጋር መተዋወቅ፣ መነጋገር፣ አብሮ መስራት፣ የነሱን አመለካከት መረዳት፣ ከሴታዊት ሰራተኞች ጋር መተዋውቅና አመለካከታቸውንም መስማት በጣም የምፈልገው ነገር ነበር። ሴታዊት ወዴት መሄድ እንደምትፈልግ የሴታዊትን አላማ በደንብ ማወቅና ድጋፍ መስጠት እፈልጋለሁ። ከዛም ባሻገር የተባባሪ ድርጅቶችን አስተሳሰብ ማወቅ ለእኔ መማሪያ እድል ነው። የሴታዊት ፌሚኒዝም አካታችነትና ሁሉን ያማከለ (ኢንተርሴክሽናል) ይመስለኛል። ይህ ለእኔ የፆታ እኩልነትን ለመፍጠር አስፈላጊና ዋነኛው ነው።

ለእኔ ፌሚኒዝም ማህበራዊ ንቅናቄ ከመሆኑም ባሻገር ስለ መምራት ነው ብዬ አስባለሁ። እስካሁን ያገኘሁትን ተሞክሮ ለሴታዊት በማቅረብ፣ ለየት ያለ እና ተጨማሪ አስተሳሰብ ለማምጣት ይቻለኝ ዘንድ የበኩሌን አደርጋለሁ። በዚህ የጋራ መድረክ ላይ መሳተፍ ከእኔ ፌሚኒዝም ጋር የሚገናኝ ይመስለኛል።