የ16 ቀናት የፀረ-ጾታዊ ጥቃት ዘመቻ #“አሁንም አልረፈደም!” የ2015 ሴታዊት ንቅናቄ መልዕክት

ሴታዊት የፆታ እኩልነት ተሟጋች ንቅናቄ ስትሆን አላማዋ በኢትዮጵያ ከጾታዊ ጥቃት ነጻ የሆነ ፍትሃዊ ማህበረሰብ ተፈጥሮ ማየት ነው። ሴታዊት ይሄንን ራዕይ እውን ለማድረግ የተለያይዩ የሴቶች መብቶች ላይ የሚያተኩሩ ጥናታዊ ጽሁፎች እና የውይይት መድረኮችን ታዘጋጃለች። በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ጾታ ላይ ያተኮሩ የተዛቡ እሳቤዎችን ለማስወገድ ስልጠናዎችን እና ዘመቻዎችን እንደአስፈላጊነቱ ታካሂዳለች፤ እንዲሁም ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች የስነልቦናና ማህበራዊ ድጋፍ አገልግሎት ትሰጣለች።
ሴታዊት በሀገራችን ላለፉት ሁለት አመታት ሲካሄድ የቆየውን ግጭት አስመልክታም በተደጋጋሚ በግልና ከሌሎች የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን በጦርነቱ ሴቶች በተለየ ሁኔታ ተጎጂ መሆናቸውን እና ፆታዊ ጥቃት የጦርነት መሳሪያ መደረጉን በመቃወም የጦርነት ይቁም ጥሪዎችን ስታሰማ ቆይታለች። በአሁን ወቅት የታየው ስምምነት ትልቅ ስኬት ቢሆንም በጦርነቱ ወቅት ለተፈጸሙ የእድሜ ገደብ የሌለውና ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጾታዊ ጥቃት የፈጸሙ አካላት ተገቢውን የህግ ቅጣት አላገኙም። በተጨማሪም ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች አስፈላጊውን የህግ፣ የሀክምና እና የስነልቦና ድጋፍ ሳያገኙ ቆይተዋል።
ሴታዊት በዚህ የ16 ቀናት የፀረ-ጾታዊ ጥቃት ዘመቻ ለኢትዮጵያ ሴቶች ድምጽ ለመሆን በማሰብ “አሁንም አልረፈደም!” ስትል፡
1. በግጭቱ ወቅት ጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች አስፈላጊውን የህክምናና የህግ አገልግሎት እንዲያግኙ፤
2. የኢትዮጵያ መንግስት ከፆታዊ ጥቃት የተረፉ ሴቶችና ህፃናትን ሙሉ በሙሉ ለመደገፍ ጥረቱን እንዲያፋጥን፤
3. ጾታዊ ጥቃት የፈጸሙ አካላት ከህግ ፊት ቆመው ተገቢው ፍርድ እንዲበየን፤
4. የሃገራችን የወንጀል ሀግ በተለየ ሁኔታ በጦርነት ወቅት የሚፈጸሙ ጾታዊ ጥቃቶችን ወንጀልነትን የሚደነግግ የህግ ማዕቀፍ እንዲያስቀምጥ፤
5. ከጾታዊ ጥቃት ፈጻሚ ጎን ለሚቆሙ የማህበረሰብ አካላት ምንም አይነት የመታገስ ባህል እንዲቀር፤

ሁሉም ባለድርሻ አካላት ይህንን መልእክት በመጋራት እንዲያተላልፉና ችግሮቹን ለመቅረፍ የበኩላቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ ታስተላልፋልች። እነዚህ 16 ቀናት ጾታዊ ጥቃትን ለመቃወም ያለንን ቁርጠኝነት የምናሳይበትና የምናረጋግጥበት እንዲሆን ሴታዊት ንቅናቄ ትሳስባለች።
#“አሁንም አልረፈደም!”


የዚህ ጥሪ ፈራሚ ድርጅቶች የሚከተሉት ነን፣

 1. ሴታዊት ንቅናቄ
 2. የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (CARD)
 3. የኢትዮጵያ ሚድያ ሴቶች ማህበር (EMWA)
 4. ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ (AHRE)
 5. ኢንተር አፍሪካ ግሩፕ – ኢትዮጵያ (IAG)
 6. አድቮከሲ ሴንተር ፎር ዲሞክራሲ ኤንድ ድቨሎፕመንት (ACDD)
 7. የሴቶች ህብረት ለሰላምና ለማህበራዊ ፍትህ (WAPS)
 8. የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር (EWLA)
 9. የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች (LHR)
 10. የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል (EHRDC)
 11. የኢትዮጵያ ሴት ሀኪሞች ማህበር (EMeWA)
 12. ትምራን (Timran)
 13. ኢትዮጵያን ዉሜን ራይትስ አድቮኬት (EWRA)
 14. የኢትዮጵያ ሰራተኞች መብቶች ተሟጋች (ELRW)
 15. Strategic Initiative for Women in the Horn of Africa (SIHA)
 16. ኢምፓቲ ፎር ላይፍ ኢንትግሬትድ ደቨሎፕመንት አሶሲዬሽን (ELiDA)
 17. Addis Powerhouse

Privacy Preference Center