የሴት እጩዎች የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ላይ ውይይቶች ተካሂደዋል 

በአስማ ነቢል

Empathy for Life Integrated Development Association (ELiDA) የተሰኘው ድህነትን ለመዋጋት በሴቶች ተቋቁሞ የሚመራው ድርጅት ባካሄደው የሴት እጩዎች እና የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ላይ በተደረገ የውይይት መድረክ ላይ ወ/ሮ ቆንጂት ብርሀኑ ምርኮኛ መፅሀፍ ደራሲ እና የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (የኢህአፓ) አባል በሰጡት የመክፈቻ ንግግር ላይ በአሁኑ ጊዜ ህብረተሰቡ የምርጫ ቅስቀሳ ላይ ያለው ግንዛቤ እና ምላሽ ከያን ጊዜው በተለየ ሁኔታ እንደሄደ ገልፀዋል። በተጨማሪም በማንኛውም ጊዜ ግን የሴቶች ጠንካራ እና ንቁ ተሳትፎ ለፖለቲካ ዋነኛው የጀርባ አጥንት መሆኑን አስረድተዋል፤ የትኛዋም ሴት ወደኋላ ሊያስቀራት የሚችለውን አበክራ እንድትቋወምና እንድትታገልም መክረዋል። 

በግልፅ የሚታየው አንድ እውነታ ማህበረሰባችን የሴት ልጅ ምርጫ በፖለቲካው መድረክ መውጣት እና ባል ከቤት ሆኖ ሴት ለፖለቲካ እንቅስቃሴ መሳተፉን እንደማይፈቅድ ሀላፊነቱን ከቤቴ ሆኖ መቀበልን እንደሚፈራ ሆኖም ግን ያህ መሆን እንደሌለበት እና እሱም በእኩል ሀላፊነት መውሰድ እንዳለበት ገልፀዋል።

በውይይቱ ወቅት የምርጫው ተሳታፊ ከነበሩት አካላት እንደተገለፀው የምርጫ ቅስቀሳ ሂደቱ ላይ ከቦታ ቦታ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ ሴት በመሆናቸው ብቻ የፖለቲካ አላማውን በዘነጋ ሁኔታ ለተለያዪ አላስፈላጊ የቃላት ውርወራዎች ተዳርገው እንደነበር ገልፀዋል። በተጨማሪም የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻው 20% ያህል የአየር ሰዓቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚያቀርቧቸው ሴት እጩዎች ቁጥር የተወሰነ እና ለሴቶች እንዲሁም የአካል ጉዳተኞች የተሰጠ የአየር ሰዓት የነበረ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች እንዳልተጠቀሙበት ገልፀዋል።

ስለነዚህ ውይይቶች ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይገኛል

Privacy Preference Center