ከሴታዊት አዲስ ቦርድ አባል ሃና ለማ ጋር ጥቂት ቆይታ

የሴታዊት አዲስ ቦርድ አባልን እንተዋወቅ! 

ሀና ለማ እባላለው። የሴቶች መብት ተሟጋች እና የጥናት ተመራማሪ ነኝ። የአዲስ ፓወር ሃውስ ዲጂታል ፌሚኒስት ጋዜጣ አንዷ መስራች ነኝ። በአዲስ ፓወርሃውስ ጋዜጣ በኢትዮጵያ የሴቶች መብት ንቅናቄዎችን እና ተሟጋቾችን ድምፅ ለማጉላት የበኩላችንን እናደርጋለን። ወጣቶችን በፆታ እኩልነት ምክክሮች ላይ ተሳታፊ ማድረግ ደግሞ ሌላኛው ስራችን ነው። በኢንክሉዶቬት የጥናት ተቋም ውስጥ የሥርዓተ -ፆታ ምርምር ሰራተኛ ሆኜ እየሰራሁ እገኛለው። የ1993 የኢትዮጵያ ሴቶች ፖሊሲ ክለሳ ውስጥ ከተሳተፉት ተመራማሪዎች አንዷ ሆኜ መስራቴ ከምኮራባቸው አስተዋፅኦዎች አንዱ ነው። የምሰራቸው እና የምሳተፍባቸው ስራዎች በፆታ እኩልነት ላይ የሚያመጡትን ለውጥ ማየት እንደ አንድ የህይወት አላማዬ እቆጥረዋለው። የሴታዊት የቦርድ አባል መሆንን በደስታ ከተቀብልኩባቸው ምክንያቶች አንዱ፣ ድርጅቱ በሴቶች ሕይወት ላይ ያለውን አዎንታዊ ተፅኖ የማየት ዕድል ማግኘት በመቻሌ ነው።

 

የሴታዊት ቦርድን ለመቀላቀል እንዴት ወሰንሽ? 

ይህንን ያደረኩበት ምክንያት ሴታዊት የምታካሂዳቸው ፕሮጀክቶች እና እንቅስቃሴዎች ሁልጊዜ በጣም የማደንቃቸው ናቸው።  ለምሣሌ ፡- “ምን ለብሳ ነበረ” እና “አሪፍ አባት“ መጀመሪያ በአእምሮዬ የሚመጡት ናቸው። ብዙ ጊዜ ፕሮጀክቶች ሲካሄዱ ፕሮጀክቱን ማስፈፀም ወይም ይህን ያህል ሰው ተረዳ ወይም ያን ያህል ሰው ዝግጅቱ ላይ ነበር ለማለት ነው እንጂ እኔ እንዳየሁት የእውነት የሰዉን አመለካከት መለወጥ ላይ አይሠራበትም። የሴቶች እኩልነትን በቀላሉ የማህበረሰቡን አመለካከት በሚቀይር ሁኔታ በደንብ መሰራት እንዳለበት “በምን ለብሳ ነበረ” እና “አሪፍ አባት” ማየት ችያለሁ። ሰዎች ስለ አስገድዶ መድፈር፣ የአስገድዶ መድፈር ባህል ስላላቸው አመለካከት እና ስለ አባትነት በአጠቃላይ እንዴት አመለካከታቸውን እንደተለወጠ በሴታዊት ማየት ችያለሁ፤ በዚህም የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል እንድሆን ዶ/ር ሲህን ስትጠይቀኝ በጣም ደስተኛ ነው የሆንኩት።

 

አዲስ የሴታዊት ቦርድ አባል እንደመሆንሽ መጠን ስራው ላይ ምን ትጠብቅያለሽ? 

መጀመሪያ ላይ እንደጠቀስኩት የሴቶች መብት ተሟጋች ነኝ ከዛ በተጨማሪም የስርዓተ ፆታ ምርምር ጥናት ሠራተኛ ነኝ እና ሁለቱንም መሆኔ ይጠቅመኛል ብዬ የማስበው ምን አይነት ፌምኒስት ወይም የሴቶች መብት ተሟጋች መሆን አለብን የሚለውን ነገር መረጃ ላይ በተመረኮዘ መልኩ (Evidence-based activity) ለመምራት ነው ። ሴታዊት ላይም በጣም የማነበው ነገር ይህንን ነውየሴታዊት ቦርድ ስቀላቅል ተመሳሳይ የሆነ ዓላማ ወይም አቋም አለን ብዬ ማሰቤ ልክ እንደሆነ ተረድቻለው። 

ሌሎች የቦርድ አባላትም ለሴቶች መብት እስካሁን ድረስ ያደረጉትን አስተዋጽዖ ሆኖም ሰፋ ባለ ሁኔታ  ሃገሪቷ ላይ ላለ ለውጥ መምጣት ከፍ ያለ ተሳታፊነት ያላቸው ናቸው። ከነሱ ጋር መተዋወቅ፣ መነጋገር፣ አብሮ መስራት፣ የነሱን አመለካከት መረዳት፣ ከሴታዊት ሰራተኞች ጋር መተዋውቅና አመለካከታቸውንም መስማት በጣም የምፈልገው ነገር ነበር። ሴታዊት ወዴት መሄድ እንደምትፈልግ የሴታዊትን አላማ በደንብ ማወቅና ድጋፍ መስጠት እፈልጋለሁ። ከዛም ባሻገር የተባባሪ ድርጅቶችን አስተሳሰብ ማወቅ ለእኔ መማሪያ እድል ነው። የሴታዊት ፌሚኒዝም አካታችነትና ሁሉን ያማከለ (ኢንተርሴክሽናል) ይመስለኛል። ይህ ለእኔ የፆታ እኩልነትን ለመፍጠር አስፈላጊና ዋነኛው ነው።

ለእኔ ፌሚኒዝም ማህበራዊ ንቅናቄ ከመሆኑም ባሻገር ስለ መምራት ነው ብዬ አስባለሁ። እስካሁን ያገኘሁትን ተሞክሮ ለሴታዊት በማቅረብ፣ ለየት ያለ እና ተጨማሪ አስተሳሰብ ለማምጣት ይቻለኝ ዘንድ የበኩሌን አደርጋለሁ። በዚህ የጋራ መድረክ ላይ መሳተፍ ከእኔ ፌሚኒዝም ጋር የሚገናኝ ይመስለኛል።

Privacy Preference Center