በታቀደዉ የሽግግር ፍትህ ሂደት ዙርያ ከሴታዊትና አጋሮችዋ የተሰጠ ረቂቅ የአቋም መግለጫ መጋቢት 2016

1. የሽግግር ፍትህ ስርዓቱ ከመጀመሩ በፊት የሽግግር ፍትህ ሂደቱን ለማካሄድ አመቺ እና አስቻይ ሁኔታዎች መፈጠር
መቻል አለበቸው ።
1.1. በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄዱ ያሉ ግጭቶች በቅድሚያ ሊቆሙ ይገባል።
1.2. የህዝብ ግልጋሎት መስጠት ያቆሙ መሰረታዊ የአገልግሎት መስጫዎች ወይም የመንግስት ተቋማት ስራ
ሊጀምሩ ይገባል።
1.3. በግጭት ሳቢያ ለመፈናቅል የተጋለጡ ህዝቦች ወደ ቅያቸው ሊመለሱ እና ለመልሶ ማቋቋም አመቺ እና
አስቻይ ሁኔታ ሊሟላላቸው ይገባል።
2. የሽግግር ፍትህ ሂደት ዘላቂነት ያለው ሰላም እና ፍትህ ለማምጣት የሚካሄድ ስርዓት እንደመሆኑ መጠን አፋጣኝ
ምላሽ ለመስጠት የሚካሄዱ ጉዳዮቸ ላይ የተመረኮዘ ሊሆን አይገባም።
3. ከታጣቂ ሃይሎች ጋር እየተካሄዱ ያሉ ስምምነቶች ለማህበረሰቡ ግልጽ እና ተዓማኒነት ሊፈጥሩ ይገባል።
4. ለግጭቶች እና የተለያዩ ማህበረሰባዊ ችግሮች መፈጠር በተለያየ መልኩ ወሳኝ እና ጉልህ ሚና ሲጫወቱ የነበሩ
አካላት በሽግግር ፍትህ አፈጻጸም ሂደቱ ላይ ግልጽ እና ውስን ሚና ሊኖራቸው ይገባል።
5. የሽግግር ፍትህ ሂደቱ ላይ የሲቪል ማህበረሰብ አካላት በበቂ ሁኔታ ክትትል እና ግምገማ የማካሄድ ጉልህ ሚና
እንዲጫወቱ የሚያስችል ድርሻ ወይም ሃላፊነት ሊሰጣቸው ይገባል።
6. የፍትህ ሚኒስቴር፣ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና የሲቪል ማህበረሰብ ካውንስል በአቻነት ከሚቋቋመው የሽግግር
ፍትህ ኮሚሽን ጋር በጋራ ሊሰሩ ይገባል።
7. ፖሊሲው በወንጃል ተጠያቂነት ዙሪያ ጉልህ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ላይ ያተኮረ ምርመራ እና ክስ ይካሄዳል ሲል
ጉልህ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በግልጽ እና ውስን አተረጓጎም ሊኖረው እና ተጠያቂነትን በአግባቡ ለማስፈን
የሚያስችል መሆን አለበት።
8. ህጻናት ፣ አካል ጉዳተኞች ፣ አረጋውያን እና አካል ጉዳተኛ ሴቶች እንደ አንድ ቡድን ሳይፈረጁ በተናጠል እና በልዩ
ሁኔታ ጉዳዮቻቸው በሽግግር ፍትህ ሂደት ውስጥ ሊታዩላቸው ይገባል።
9. የአለም አቀፍ ማህበረሰብ አካላት በሽግግር ፍትህ አፈጻጸም ሂደቱ ላይ ተሳታፊነታቸው በተለያየ መልኩ ማለትም:
በሙያ፣ በምርመራ፣ ክትትል እና ግምገማ ረገድ የተረጋገጠ ሊሆን ይገባል።
10. የህግ እና ተቋማት ማሻሻያ አውድ ስር
10.1. የህግ ማዕቀፉ በግጭት ወቅት የተፈጸሙ ወንጀሎችን ተጠያቂነት መሰረት ያደረጉ ህጎች ማሻሻያ ባለፈ
ሌሎች የህግ ግድፈቶች ሊያስተካከል እና ሁሉን ተኮር ዘላቂ እና ወሳኝ ለውጥ ሊያደርግ ይገባል።
10.2. በጦርነትም ሆነ በሰላሙም ወቅት የሚፈጸሙ የሴቶች መብት ጥሰቶችን ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ
ለሴቶች ዘላቂ የመብት ከለላ የሚሰጡ ህጎች ሊጸድቁ ይገባል።
10.3. ከመከላከያ እና ሌሎች ተቋማት በዘለለ ለሴቶች እንዲሰሩ የተቋቋሙ ተቋማት ሊሻሻሉ ይገባል።
10.4. ተቋማት ሃላፊነታቸውን በአግባቡ የሚወጡ ሊሆን ይገባል።
10.5. ተፈናቃዮችን መልሶ ማቋቋምን በሚመለከት ራሱን የቻለ ተቋም ሊቋቋም ይገባል።
11. ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተመለከት የሴቶች መብትን ማስከበር እስከቻለ ደረስ ብቻ ተፈጻሚነት ሊኖራቸው
ይገባል።
12. በግጭት ሳቢያ የተፈጸሙ ጾታዊ እና ወሲባዊ ጥቃቶች ከወንጀል ተጠያቂነት ባለፈ በካሳ ሊያዙ አይገባም።
12.1. ጾታዊ ጥቃት የተፈጸመባት ሴት ዘላቂ የሆነ ምላሽ እና የተሟላ ፍትህ እና ካሳ ልታገኝ ይገባል ይህም
የኢኮኖሚ ማብቃት፣ መልሶ ማቋቋም እና የደረሰባቸውን የስነልቦና እና የአእምሮ ጤና መታወክ ከግምት
ውስጥ በማስገባት የስነልቦና ድጋፍን ይጨምራል።
13. በመንግስት አካላት ሴቶች ላይ በግጭት ሳቢያ ለተፈጸሙ ጥቃቶች እውቅና ሊሰጥ እና ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል።
14. በሽግግር ፍትህ አፈጻጸም ሂደቱ ላይ ሊወያዩ እና በሽግግር ፍትህ ሂደቱ ላይ ሁሉም ታጣቂ ሃይሎች የተብራራ እና
ግልጽ ተሳትፎ ሊኖራቸው ይገባል።
15. የሽግግር ፍትህ ሂደቱ አጽንዖት በመስጠት በግጭት ሳቢያ ሴቶች ላይ የተፈጸሙ ጾታዊ ጥቃቶች ዳግመኛ ሊፈጸሙ
እንደማይችሉ ዋስትና ሊሰጥ ይገባል።
16. መዘክር እና መታሰቢያን ባስመለከተ በሁሉም ግጭት የተፈጸመባቸው አካባቢዎች ተመሳሳይ እና ህዝቡ ለደረሰበት
ጉዳት ምላሽ ሰጪ ወሳኝ ተቋማትን ሊቋቋሙ ይገባል።
17. በሃገሪቷ የግጭት መንሳኤ የሆኑ የትርክት እንዲሁም መዋቅራዊ ችግሮች ህጋዊ እና ተቋማዊ የእርምት ማስተካካያ
እና እርምጃ ሊደረግባቸው ይገባል።
18. የሽግግር ፍትህ ሂደቱ ውስን እና ግልጽ የጊዜ ወሰን ሊኖረው እና ሂደቱም በተወሰነ የጊዜ ገደብ ሊገመገም ይገባል።
19. የሽግግር ፍትህ ሂደቱ ኮሚሽኑን ሲያዋቅር ከይስሙላ ያለፈ አካታችነት እንዲኖረው ግልጽ እና አስገዳጅነት ያለው
የምልመላ ሂደት ሊኖረው ይገባል።
20. በጦርነቱ ሳቢያ ወሲባዊ ጥቃት የተፈጸመባቸው ተጠቂዎች እንደ አንድ ቡድን ተይዘው በሽግግር ፍትህ ሂደቱ ላይ
ቀጥተኛ ተሳታፊ ሊሆኑ እና ጉዳዮቻቸው በልዩ ሁኔታ ሊያዝ ይገባል።

Privacy Preference Center